Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶችና ሴቶች ሊግ የ19 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶችና ሴቶች ሊግ በወሎ ግንባር ለሚገኙት የጸጥታ ሀይሎችና ተፈናቃዮች ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ድጋፎችን አስረከበ፡፡

“ወጣቱ ትውልድ በህልውና ዘመቻው ግንባር ሄዶ ከመሠለፍ ባለፈ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቃይ ወገኖች ድገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶችና ሴቶች ሊግ ገለጸ፡፡

ጽህፈት ቤቱ ይህን ያለው በወሎና አፋር ግንባር ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚኒሻ እንዲሁም ለተፈናቃዮች ድጋፍ ባደረገበት ወቅት ነው፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶችና ሴቶች ሊግ ኃላፊ አቶ አክሊሉ ታደሰ÷ ወጣቱ ለሃገር መስዋዕትነትን ከመክፈል ባለፈ ለወገን ደራሽነቱን እያሳየ ነው ብለዋል፡፡

በወሎ ግንባር ለሚገኙት የጸጥታ ሀይሎችና ተፈናቃዮች ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ድጋፎችንም አስረክበዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ሊጉ በአፋርና ወሎ ግንባር ግምታቸው 38 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የምግብ፣ መጠጥና አልባሳት ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡

የፓርቲው የሴቶች ሊግ ሀላፊ ወይዘሮ መስከረም አበበ በበኩላቸው÷ ወጣት ሴቶች ከግንባር እሰከደጀን ለህልውና ዘመቻው እያደረጉት ያለው ተጋድሎ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

“ለወገን ደራሽ ወገን ነው” በማለት ለጸጥታ ኃይሉና ለተፈናቃይ ወገኖች የአይነት ድጋፋቸውን ለግስዋል ብለዋል፡፡

የህልውና ዘመቻው እስኪጠናቀቅም ድጋፉ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡

በከድር መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.