Fana: At a Speed of Life!

ሆስፒታሉ ግማሽ ሚሊየን ብር የሚገመት የነፃ ህክምና አገልግሎት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ጠቅላላ ሆስፒታል ለማህፀን ውልቃት ህመምተኞች ነፃ ህክምና አገልግሎት ሰጥቷል።

ነፃ የህክምና አገልግሎቱ ሆስፒታሉ ከዊንግስ ኦፍ ሂልስ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ማዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

የማህፀን ውልቃት ህመም በተለይም በገጠሩ የኢትዮጵያ ክፍል እንደሚበዛ የተናገሩት የሐረማያ ጠቅላላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተረ ዶክተር ሰለሞን ዘሪሁን በዚህም ከተለያዩ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ወረዳዎች ለተወጣጡ 150 ህሙማን አገልግሎቱን መሰጠት ማስፈለጉን ገልፀዋል።

በአማራ፣ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ዊንግስ ኦፍ ሂልስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ የማህፀን ውልቃት ህመምን አስመልክቶ ግንዛቤው ያነሰ በመሆኑ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ህመሙ ከባድ ዕቃዎችን መሸከምን ጨምሮ የተመጣጠነ ምግብ ባለመመገብ እንደሚከሰት የተናገሩት የድርጅቱ ፕሮግራም ዘርፍ አስተባባሪዋ ዶክተር ፌበን ገብረእግዚአብሄር በዚህም ምክንያት ከነፃ ህክምናው በተጨማሪ የስንዴና ሩዝ ድጋፍ ማድረግ ማስፈለጉን ገልፀዋል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.