Fana: At a Speed of Life!

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች “ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች “ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄን ተቀላቅለዋል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ኢትዮጵያ በአለም አደባባይ ያላትን ተቀባይነትና ገጽታ ለማበለሻት ግንባር ፈጥረው እየተንቀሳሰቀሱ ያሉ ሃይሎችን ለመቀልበስ ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት በሚል በተዘጋጀው ዘመቻ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራርና ሰራተኞች ላሳዩት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

እውነት እስካልተነገረ ድረስ ማሸነፍ አይቻልም ያሉት አቶ መላኩ÷ በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ጥቃት የፈጸሙ አሸባሪ ኃይሎች የኢትዮጵያን ገጽታ ለማበላሸት በሚያደርጉት እንቅስቀሴ ሁላችንም ዘማቾች ካልሆንን ውሸት እውነት ሆኖ አገርን ይጎዳል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ እውነታውን ማወቅ ያለበት ነጩ ቤተ-መንስግስት ላይ ያለው አካል ብቻ ሣይሆን የአለም ህዝብ በመሆኑ እውነቱን በማሳወቅ ለሀገራችን ዘብ መቆም ይገባል ሲሉ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.