Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለጤና አገልግሎት ችግር ተዳርገዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ እና አፋር ክልሎች ጁንታው በጤና ተቋማት ላይ ባደረሰው ጥፋት ከ1ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለጤና አገልግሎት ችግር መዳረጋቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት ምክንያት በጤና ተቋማትና መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት ማድረሱን ገልጸዋል፡፡
በአማራ ክልል አምስት ዞኖች ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች እና ጤና ኬላዎች ሙሉ በሙሉ በሽብር ቡድኑ ተዘርፈዋል፤ ወድመዋል፤ አገልግሎቱም ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ብለዋል የጤና ሚኒስትሯ፡፡
በአፋር ክልል በዞን አንድ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል እንዲሁም ተሽከርካሪዎች ተዘርፈዋል ብለዋል፡፡
በዚህም በአማራ ክልል 1 ነጥብ 8 ሚሊየን እንዲሁም በአፋር ክልል 112 ሺህ ዜጎች ለጤና አገልግሎት ችግር መዳረጋቸውን ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡
የጤና አገልግሎቱ በተቋረጠባቸው አማራና አፋር ክልልሎች ተንቀሳቃሽ የጤና አገልግሎት ለመስጠት በርካታ ባለሙያዎች ወደ ስፍራው መላካቸውንም አስታውቀዋል፡፡
በአካባቢው የመድሃኒት እጥረት እንዳይፈጠርም ግብዓቶች እየተሰራጩ መሆኑን ዶክተር ሊያ ማስታወቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.