Fana: At a Speed of Life!

የሱዳንን ዋና መስመር በመቆጣጠር ኮሪደሩን ለማስከፈት የተመኘው ጠላት አጠቃላይ ህልሙ መክኗል – ብርጋዴር ጀኔራል ናስር አባዲጋ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳንን ዓለም አቀፍ ዋና መስመርን በመቆጣጠር ኮሪደሩን ለማስከፈት የፈለገው ወራሪው የጠላት ኃይል ህልም ከንቱ ሆኖ ቀርቷል አሉ የ8ኛ መካናይዝድ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ናስር አባዲጋ።

አሸባሪው ህውሓት በቲሃ በኩል ቁጥሩ ከ1 ሺህ 200 እስከ 1 ሺህ 400 የሚጠጋ ኃይል አስርጎ  በአራት አቅጣጫ ጦርነት በመክፈት በሽንፋ-ጭልጋ- ትክልድንጋይ  አድርጎ ጎንደርን በመቆጣጠር  አዲስ አበባ የመግባት ዕቅድ እንደነበረው  ጠቅሰው÷ ይህ ከንቱ ህልሙ እንደመከነበት ዋና አዛዡ ገልፀዋል።

አለምአቀፉን የሱዳን መስመር ለማስከፈት ጥረት ያደረገው ወራሪው ቡድን፥ ውጊያ በከፈተበት ጫካ ውስጥ እንዳልሆነ ሁኖ ቀርቷል፤ የቅዥት ህልሙም መክኗል ነው ያሉት።
ዋና አዛዡ እንዳሉት፥ በቲሃ በተካሄደው ውጊያ 462 የጠላት ኃይል ተደምስሷል፤ 39 ተማርኳል።
ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የግልና የቡድን መሳሪያዎች በወገን ሀይል ቁጥጥር ስር ውለዋል።
በዚህ ግንባር ውጊያ በተካሄደበት አካባቢ ተፈጥሮ በራሷ እገዛ ነበራት የሚሉት ብርጋዲየር ጀነራል ናስር ፥ ሽንፋ ወንዝ በርካታ የጠላት ኃይልን ጠራርጎ መውሰዱን ለአብነት ጠቅሰዋል።
የቀረውን የጠላት ኃይል የመለቃቀም ስራ ነው የቀረው ያሉት ዋና አዛዡ፥ ክፍለ ጦራቸው የትኛውንም ኃይል ድባቅ ለመመምታት የተሟላ ወታደራዊ ቁመና ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
የአካባቢው ማህበረሰብ ለወገን ጦር የሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ የሚመሰገን መሆኑን ገልጸው÷ እኛም የጀግንነትና የአሸናፊነት ወኔ ሰንቀን የአሸባሪውን ቡድን ከመደምሰሰ በተጨማሪ የኢትዮጵያን ዳር ደንበር እናስከብራለን ብለዋል።

 

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.