Fana: At a Speed of Life!

ዩኒሴፍ የድንኳን ድጋፍ ለትምህርት መምሪያው አበረከተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የመማር ማስተማሩን ተግባር ምቹ ለማድረግ ዩኒሴፍ የድንኳን ድጋፍ ለትምህርት መምሪያው አበርክቷል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትናየጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን እንደገለፁት÷ ከሰሜን ወሎ ተፈናቅለው ለመጠለያነት ሲጠቀሙበት የነበረ ትምህርት ቤቶችን ስራ ለማስጀመር ዮኒሴፍ ከ1ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት 25 ድንኳን ለትምህርት መምሪያው አስረክበዋል፡፡

ትምህርት ቤቶች መጠለያ በመሆን አገልግሎትን እየሰጡ በመሆኑ የመማር ማስተማሩን ተግባር ለማስቀጠል ለተፈናቃዮች መጠለያ በመሆን የሚያገለግል በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የደሴ ከተማ ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ እያሱ ዘውዱ በበኩላቸው÷ ትምህርት ቤቶችን ነፃ ለማድረግ 1ሺህ ድንኳን ያስፈልገናል በማለት የተደረገው ድጋፍ ጅማሮ ቢሆንም ፋይዳው ብዙ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የመማር ማስተማር ተግባሩን ለማስጀመር ትምህርት ቤቶችን የማፅዳት ቁሳቁሶችን የመጠገን ስራ ይሰራል በማለት ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ተማሪዎችንም ለማስቀጠል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀልም ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ የክልልና የፌዴራል መንግስት ትኩረት በመስጠት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪን አቅርበዋል፡፡

በሰብለ አክሊሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.