Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ከተማ ለተጠለሉ ተፈናቃዮች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ከሰሜን ወሎ ተፈናቅለው በደሴ ከተማ በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ተደረገ፡፡

መላዕከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ በመጠለያ ጣቢያ በመዘዋወር ጉብኝት በማድረግ 500 ፍራሽ እና 300 ኩንታል ዱቄት አከፋፍለዋል፡፡

በዚህም ለድጋፉ ከ2ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል፡፡

መምህር ግርማ÷ የደረሰው ጉዳት አሳዛኝ ነው በማለት ወደ ቀያችሁ ተመልሳችሁ እስክትቋቋሙ ድረስ ድጋፉ ቀጣይነት ይኖረዋል ብለዋል፡፡

አርቲስት ደሳለኝ ኃይሉ በበኩሉ÷ ይህ ሰዓት የምንደጋገፍበትና የምንረዳዳበት ጊዜ ነው ብሏል፡፡

በዚህ ጊዜም ሃላፊነቱን ያልተወጣ ባለሀብት ነገ ኢትዮጵያ የኔ ናት ማለት አይችልም በማለት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተናግሯል፡፡

በሰብለ አክሊሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.