Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የቱሪዝም ቀን በአዲስ አበባ ደረጃ ከመስከረም 12 እስከ ጥቅምት 5/2014 ይከበራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው ዓለም አቀፉ የቱሪዝም ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ከመስከረም 12 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ፋይዛ መሐመድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ42ኛ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፉ የቱሪዝም ቀንን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የቱሪዝሙን ዘርፍ ክፉኛ አዳክሞታል ያሉት ኃላፊዋ÷ የበዓሉ መከበርም በዘርፉ የተዳከመውን ኢኮኖሚያለማነቃቃት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል ።
“ቱሪዝም ለሁለተናዊ እድገት!” በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የቱሪዝም ቀን በከተማዋ የሚገኙ የቱሪስት መዳራሻ ስፍራዎችን የማስጎብኘት፣ በልዩ ልዩ የጎዳና ላይ ትርዒቶች እና በስፖርት ቱሪዝም በመሳሰሉት ዝግጅቶች የኮቪድ19 ወረርሽኝ ፕሮቶኮልን በጠበቀ መልኩ እንደሚከበርም በመግለጫው መመላከቱን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.