Fana: At a Speed of Life!

በኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ስም የተሰየመ አደባባይ የፊታችን እሁድ ይመረቃል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ስም የሚሰየመውን አደባባይ የፊታችን እሁድ እንደሚመረቅ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌደሬሽንና የለሚ ኩራ ክፍል ከተማ አስታወቁ ።
የመዲናዋ አትሌቲክስ ፌደሬሽንና የክፍለ ከተማው አመራሮች በጋራ በሰጡት መግለጫ በአፍሪካ የመጀሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት ሴት የኦሊምፒክ ባለድል በመሆን የበርካታ አትሌቶች የጀግንነት ምሳሌ ለሆነችው ኮማንደር አትሌት ደራርቱ አደባባይ መሰየሙ እንደሚያስደስታቸው ገልጸዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሊያስ ሙሀመድ፤ በጀግናዋ አትሌት ስም በክፍለ ከተማችን አደባባይ በመሰየሙ እንኮራለን ብለዋል።
እንደ ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ አይነት ዓለም አቀፍ ጀግኖችን ማክበር ሌሎች ጀግኖችንምለማፍራት ያግዛል ብለዋል።
በመሆኑም በጀግናዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ስም የተሰየመው አያት የሚገኘው አደባባይ የፊታችን እሁድ በይፋ ይመረቃል ብለዋል።
ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ተሉ እኤአ በ1992 የባርሴሌና ኦሊምፒከም በ10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ በማምጣት ለሴት ጥቁር አፍሪካዊያን ፈር ቀዳጅ አትሌት ናት።
በሲዲኒ ኦሊምፒክም ለኢትዮጵያ ወርቅ አምጥታለች፤ ከዚህም ባለፈ በርካታ ድሎችን በማስመዝገብ ስሟ በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ ይጠራል።
ፍልቅልቋ አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ አሁን ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዚዳነትነት እየመራች እንደምትገኝም የኢዜአ ዘገባ አውስቷል።
በእለቱ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ ዓላማ ያደረገ የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ይካሄዳል ተብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
30
Engagements
Boost Post
29
1 Share
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.