Fana: At a Speed of Life!

መስከረም 20 ለሚከናወነው ምርጫ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መስከረም 20 ለሚከናወነው ምርጫ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ቦርዱ የዝግጅት ሂደቱን በተመለከተ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በተራዘመው ሁለተኛው ምርጫ 7 ነጥብ 6 ሚሊየን ህዝብ እንደሚሳተፍበት የገለጹት የቦርዱ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ ሶልያና ሽመልስ÷ ምርጫውን ለማከናወን ቦርዱ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
ይህንን ምርጫ ለማካሄድ 30 ሺህ የሚጠጉ የምርጫ አስፈጻሚዎች መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል፡፡
በደቡብ፣ ሱማሌ እና ሀረሪ ክልሎች መስከረም 20 በሚደረገው ምርጫ 47 ለክልል ምክር ቤት 105 ደግሞ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተዘጋጁ ምርጫ ክልሎች መኖራቸውንም አማካሪዋ ተናግረዋል፡፡
22 የፖለቲካ ፖርቲዎች የሚሳተፉ ሲሆን÷ 1 ሺህ 236 እጩዎች በምርጫው መቅረባቸው ተገልጿል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ህዝበ ውሳኔውም በተያዘለት ቀን መስከረም 20 አብሮ የሚከናወን መሆኑም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.