Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያውያንን የመልማት መብት እንደምትደግፍ ቻይና ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገሪቷን ፓርላሜንታዊ ምርጫ የተባበሩት የሩሲያ ፓርቲ በከፍተኛ ድምፅ ማሸነፉን ተከትሎ ቻይና ሩሲያውያን ለመልማት የሚከተሉትን መንገድ እንደምትደግፍ አስታወቀች፡፡

የሩሲያ ሀገረ መንግስታዊ ምርጫ በዜጎቿ ፖለቲካዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው፤ ውጤቱም የሩሲያውያንን ፍላጎት ያመላከተ ነው ሲሉ የሩሲያ ቃል አቀባይ ዛሆ ሊጂያን ተናግረዋል፡፡

በተካሄደው የድምፅ ቆጠራ ከተቆጠረው 98 በመቶ የምርጫ ድምፅ መስጫ ወረቀት ውስጥ 50 በመቶ የሚጠጋውን የተባበሩት የሩሲያ ፓርቲ አግኝቶ ማሸነፉን የሩሲያ ማዕከላዊ ምርጫ ኮሚሽን በዛሬው ዕለት አሳውቋል፡፡

ተፎካካሪው ኮሙኒስት ፓርቲ ከ20 በመቶ ያነሰ ድምፅ ማግኘቱንም ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡

ከምርጫው ውጤት በኋላ ቻይና ባስተላለፈችው መልዕክት÷ በቭላድሜር ፑቲን የሚመራው መንግስት አዲስ መሻሻሎችን ለማስመዝገብ፣ እድገትና ብልፅግናን እውን ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት በፅኑ እደግፋለሁ ብላለች፡፡

ከምርጫው በኋላ የቻይና የሕግ አውጪ አካላት ከሩሲያ ጋር ከምን ጊዜውም በላቀ የትብብር መንፈስ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸው ነው የተገለፀው፡፡

ምንጭ ÷ ሽንዋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.