Fana: At a Speed of Life!

50 ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች በሜዲትራኒያን ባህር ሰጠሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)50 ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች በሜዲትራኒያን ባህር ሰጥመው ህይዎታቸው ማለፉን የሃገሪቱ መንግስት አስታውቋል፡፡

የሱዳን ባለሥልጣናት እንደገለጹት ስደተኞቹ በአዘዋዋሪዎች በህገወጥ መንገድ ሲጓዙ ከነበሩ 4ሺህ 850 ስደተኞች መካከል ሱዳናውያን ፣ ሶሪያውያን ፣ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን መካከል ይገኙበታል፡፡

መቀመጫውን ካርቱም ላይ ያደረገው የደቡብ ሱዳን ተሟጋች አኮል ማሎንግ ጠቅሶ የአይ ሬዲዮ እንደዘገበው ስደተኞቹ ወደጣልያን የሚያቀኑ ሲሆን÷ ዕድሜያቸውም ከ15 እስከ 35 እንደሚገመት ነው ዘገባው የሚያመላክተው፡፡

መነሻቸውን ሊቢያ ያደረጉት ስደተኞቹ ወደጣልያን በማቅናት ላይ ሳሉ ነው ጀልባው በሜዲትራንያን ባህር ሊሰምጥ የቻለው፡፡

በዚህም የ50 ደቡብ ሱዳናውያን ህይዎት ሲያልፍ፣ 280 የሚሆኑ ስደተኞች በጣልያን ሆስፒታሎች ህክምናቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን አክቲቪስት አክለውም ሟቾቹ ባለፈው ሳምንት ወደ አውሮፓ ከተሻገሩ 1 ሺህ 350 የደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች መካከል መሆናቸውን ገልፀው÷ በአሁኑ ጊዜ ወደጣልያን የተሻገሩ 285ቱ ስደተኞች ሲሲሊ በሚገኘው የጣሊያን ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።

ምንጭ፡- ሱዳን ፖስት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.