Fana: At a Speed of Life!

ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች አካታች የሆነ የበይነ መረብ ግንኙነት እንዲኖር እየተሰራ ነው- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች አካታች የሆነ የበይነ -መረብ ግንኙነት እንዲኖር ኢትዮጵያ በትኩረት እየሰራች መሆኑን ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡
“ወደ አዲስ ጉዞ” በሚል በዓለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት አዘጋጅነት ላለፈው አንድ አመት ሲካሄድ የነበረው የመጀመሪያ ምዕራፍ ጉባኤ ማጠቃለያ በበይነ መረብ ተካሂዷል፡፡
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፥ የኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል ለግሉ ዘርፍ ክፍት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ፈጣን የበይነመረብ ግንኙነት ለሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ ኢትዮጵያ እየሰራች ነው ያሉት ፕሬዝዳንቷ፥ አካታች የሆነ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችል የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ቀርፃ ተግባራዊ እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የተለያዩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን እያደረገች መሆኑን ያነሱት ፕሬዝዳንቷ ተወዳዳሪ የሆነ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገናኘ እና አካታች የሆነ የበይነ መረብ ግንኙነት መዘርጋት በቴሌኮም ዘርፍ ውስጥ ያለ ማሻሻያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስብሰባው በማደረግ ላይ ያሉ ሀገራት የበይነ መረብ ግንኙነትንና የዲጂታል ትራንስርሜሽንን ለማጠናከር፣ በቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለድርሻችን ለማገናኘት፣ አይ ሲ ቲን መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን መስጠት እና አካታች የሆነ የበይነ መረብ ግንኙነትን መፍጠርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.