Fana: At a Speed of Life!

በሀገር ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉና ያልተፈቀዱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በሀገር ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ያልተፈቀዱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የቴሌኮም ማጭበርበሪያ መሳሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዙን አስታወቀ፡፡
ኤጀንሲዉ በ2013 ዓ.ም ብቻ በተለያዩ ጉ/ቅ/ፅ/ቤቶች ስምንት የቴሌኮም ማጭበርበሪያ መሳሪያዎች ወደ ሀገር ዉስጥ ሊገቡ ሲሉ የያዘ ሲሆን በሀገር ደረጃ ሊያደርስ የነበረዉን ከ19 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ኪሳራ ማዳን መቻሉን በኤጀንሲዉ የመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂዎች ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊዉ አቶ እሸቱ ቡሬሳ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በተጠናቀቀዉ በጀት አመት የደህንነት ስጋታቸዉ ከፍተኛ የሆኑ በ14 ድርጅቶች ስም የመጡ 49 ድሮኖችና የስለላ ካሜራዎች ወደ ሀገር ዉስጥ እንዳይገቡ መከልከላቸውንም ኃላፊው ገልጸዋል።
በአሁኑ ሰዓት ወደ ሀገር ዉስጥ እንዳይገቡ ክልከላ ከተደረገባቸዉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች መካከልም የቴሌኮም ፍራዉድ መፈጸም የሚያስችል ሲም ቦክስ ፣ ስፓይ ካሜራ፣ ሳተላይት ስልክ፣ ድሮን ፣ የመገናኛ ሬዲዮ፣ ወታደራዊ ባይነኩላር እና የቅኝት መሳሪያዎች፣ ለሰቪላዊና ዎታደራዊ አገልግሎት የሚዉሉ ጂፒኤሶች፣ ድብቅ የድምፅ መቅጃ ማይክራፎኖች፣ ዱዋል ባንድ ራዉተር፣ Transmitters (fm) እና vsat ይገኙበታል ተብሏል፡፡
በመሆኑም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርት አስመጭዎች ወደ ሀገር ዉስጥ እንዳይገቡ ክልከላ የተደረገባቸውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ዓይነት በመለየት ማስመጣት እንደሚገባቸዉ ኃላፊዉ ማሳሰባቸውን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.