Fana: At a Speed of Life!

ባለሃብቶችና ነጋዴዎች 82 ሰንጋዎችን አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በምዕራብ ጎንደር ዞንና ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ በእርሻ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶችና ነጋዴዎች ግምቱ 1ነጥብ8 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 82 ሰንጋዎችን ድጋፍ አደረጉ፡፡

የቡድኑ አስተባባሪ አቶ አሰማራው መኮነን በምዕራብ ጎንደር ዞንና በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ በእርሻ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶችና ነጋዴዎች ከተሰበሰበ 1ነጥብ 8ሚሊየን ብር በሚገመት ገንዘብ 82 ሰንጋዎችን ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

አቶ አሰማራው እንደተናገሩት÷ በምዕራብ ጎንደር ዞን ግንባር በዛሬው ዕለት 30 ሰንጋዎችን ለዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ድጋፉን ማስረከባቸውን አመልክተዋል።

ከቀናት በፊት ለምዕራብ አርማጭሆ ከ20 ሰንጋ በላይ፣ አርማጭሆ ወረዳ መንገድ እንዳይዘጋ ላደረጉ አካላት አምስት ሰንጋ፣ በነገው ዕለት ደግሞ ለሁመራ ግንባር 27 ሰንጋዎች እንደሚበረከት አስተባባሪው ገልጸዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው÷ የጠላት ሀይል ድል በተደረገበት ግንባር ባለሃብቶች ተገኝተው ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ወራሪው ሃይል በገባባቸው አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ጉዳት አልደረሰም ያሉት አስተዳዳሪው የዞኑ ህዝብም ከሰራዊቱ ጀርባ ደጀን በመሆን ያሳዩት ተግባር ድንቅ ነው ብለዋል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.