Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የሚካሄደው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በሐረሪ ክልል የሚካሄደው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው÷ በክልሉ የሚካሄደው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ጃቢር አልዪ እንደገለጹት÷ በክልሉ የሚከናወነው ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር የጋራ እቅድ አውጥቶ እየሰራ ነው፡፡

በክልሉ ከሚገኙ የሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት እና የክልሉ ፖሊስና ሚሊሻ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት እያከናወኑት ያለው ስራም አበረታች ውጤት እያሳየ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በተለይ ከህግ ማስከበሩ ጋር ተያይዞ ከአሸባሪዎቹ ህውሓት እና ሸኔ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ግለሰቦችን በህግ ቁጥጥር ስር የማዋል እና ንብረቶቻቸውንም የማሸግ ሰራ መከናወኑንም መግለጻቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በአካባቢው የሚታየውን የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታን ይበልጥ ለማጠናከር እና አንዳንድ የጸጥታ ስጋት የሚታይባቸውን አካባቢዎችን ከስጋት ነጻ ለማድረግ ወቅታዊ የጸጥታ የኮማንድ ፖስት እቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል፡፡

በዚህም በክልሉ የሰላም እና የጸጥታ ስጋት የሚታይባቸው አካባቢዎችን ከስጋት ነጻ ለማድረግ እስከ መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ ም ድረስ የጸጥታ ሃይሉ በአካባቢው በመንቀሳቀስ የማጥራት ስራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል፡፡

ለዚህም ማህበረሰቡ ለጸጥታ ሃይሉ የሚያደርገውን ጥቆማ በማድረግ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.