Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ ለኤርትራውያን ስደተኞች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ለኤርትራውያን ስደተኞች ድጋፍ እንዲያደርግ አዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ጠየቁ።
ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ ስደተኞችን ማስወጣት ባለመቻሉ ስጋት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ በበኩሉ በስደተኞቹ ጉዳይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ገልጿል።
ስደተኞቹ ዛሬ በአዲስ አበባ የኮሚሽኑ የኢትዮጵያ ወኪል ቢሮ በር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።
ስደተኞቹ እንደሚሉት÷ ባለፉት ሁለት ወራት በትግራይ ክልል በተለይም ህንጻጽና ማይ-አይኒ የተባሉ የስደተኛ መጠለያዎች ለሚገኙ ኤርትራውያን ድጋፍ እየቀረበ አይደለም።
በመጠለያ ካምፖቹ የምግብ፣ የውኃ፣ የህክምና የመድሃኒት አቅርቦት ባለመኖሩ ስደተኞቹ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ተናግረዋል።
በተለይም የተለያየ የጤና ችግር ያለባቸው ስደተኞች በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ የስቃይ ጊዜ እያሳለፉ መሆኑንም ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.