Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የእጽዋት ጥበቃ ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ የእጽዋት ጥበቃ ፍኖተ ካርታ ይፋ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

እህል ተዘርቶ እስከሚሰበሰብ ባለው ሂደት በጸረ እጽዋት ተባይና ተዛማጅ በሽታዎች አማካኝነት ከ30 በመቶ በላይ የሚሆነው የግብርና ምርት እንደሚባክን ይነገራል፡፡

የእጽዋት ጤና አጠባበቅ ስራ መነሻና መድረሻው ሳይታወቅ በተበጣጠሰ መልኩ ለበርካታ ዓመታት በዘልማድ ሲተገበር ቆይቷል፡፡

ይህም ኢትዮጵያ በመጤም ሆነ ተዛማች በሆነ ጸረ እጽዋት ተባዮች አማካኝነት በርካታ ምርት ሲባክንባት መቆየቱ ተገልጿል፡፡

ይህን ችግር የሚፈታ ወጥ የሆነ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ፣ ከትላልቅ ሃገራዊ እቅዶች ጋር የተናበበና ዓላማቸውንም ሊያሳካ የሚችል የእጽዋት ጥበቃ ፍኖተ ካርታ ረቂቅ በዘርፉ በተሰማሩ ምሁራን እንዲሁም ሌሎች በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሲዘጋጅ ቆይቷል፡፡

በእለቱም የመጨረሻው ረቂቅ ሰነድ ቀርቦ ጥሪ የተደረገላቸው ምሁራን ተመራማሪዎችና ባለድርሻ አካላት ጥያቄና አስተያየት ሰጥተውበታል፡፡

ለቀረቡት ጥያቄዎች ማብራሪያ በመስጠት እንዲሁም ገንቢ አስተያየቶችን እንደግብአት በመጠቀም ሰነዱ ይፋ የተደረገ ሲሆን÷ ለአተገባበሩም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃላፊነቱን ለመወጣት መስማማታቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.