Fana: At a Speed of Life!

ለመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ እና ምስጋና መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ እና ምስጋና መርሀ ግብር በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው።
መርሀ ግብሩ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አዘጋጅነት “እግር ኳሳችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል።
የመርሀ ግብሩ ዓላማ የስፖርት ቤተሰቡ የአገር ሉዓላዊነት እና አንድነትን ለማስጠበቅ መስዋዕትነት እየከፈለ የሚገኘውን መከላከያ ሰራዊት ለማመስገን እና ድጋፉን ለማሳየት ነው።
የመከላከያ ሚንስቴር ከፍተኛ አመራር አባላት፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚዎች፣ የስፖርት ማህበረሰቡ እንዲሁም የኪነጥበብ ባለሙያዎች በመርሀግብሩ ላይ ተገኝተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.