Fana: At a Speed of Life!

የሰብዓዊ ድጋፍ ለማዳረስ ለሚደረገው ጥረት ጀርመን ዝግጁ ነች-ጉንተር ኑክ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የጀርመን መራሂተ መንግስት በአፍሪካ የግል ተወካይ እንዲሁም በጀርመን የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር የአፍሪካ ኮሚሽነር በሆኑት ሚስተር ጉንተር ኑክ ከተመራ ልዑካን ቡድን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
በሀገራችን ሰሜናዊ ክፍል በህወሓት የጥፋት ምክንያት የተፈጠረው የሰብዓዊ ቀውስ ያለበትን ደረጃ እና ወደፊት በአፋጣኝ ስለሚያስፈልገው ፈጣን ምላሽ የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ለልዑካን ቡድኑ አብራርተዋል።
በተለይም በወረራው ምክንያት በአማራና አፋር ክልሎች ከ540 ሺህ በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውንና ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ህብረተሰብ ተጎጂ መሆኑን ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን ለማቀላጠፍ በርካታ ማሻሻያዎችን በማድረግ ዝግጁነቱን ያረጋገጠ ቢሆንም÷ በአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ ድርጅቶች እየተሰጠ ያለው ምላሽ ግን ካለው ፍላጎት አንጻር እጅጉን አናሳ መሆኑን ገልጸዋል።
ሚስተር ኑክ በበኩላቸው የጀርመን መንግስት የሰብዓዊ ድጋፍ በሁሉም ጉዳት ባጋጠማቸው አካባቢዎች ለማዳረስ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የጀርመን መንግስት ዝግጁ መሆኑን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.