Fana: At a Speed of Life!

ከመሠረታዊ ባህርተኛ ተማሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ባህርዳር መኮድ ካምፕ ከሚገኙ መሠረታዊ ባህርተኛ ተማሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባህር ሃይል ም/አዛዥ ለሎጀስቲክስ ኮሞዶር ዋለፃ ዋቻ ፥ ተቋሙ በትምህርትና ሥልጠና ብቁና ፕሮፌሽናል የባህር ሃይል አባላት የማፍራት እና የክፍሉን አቅም የሚያሳድጉ ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
ባህር ሃይላችን ባለፉት አመታት የተቋማዊ ሪፎርም ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱንና በአዲሱ በጀት ዓመትም የተማረ የሰው ሃይል ለማፍራት የሚደረገው ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ጠንካራ የባህር ሃይል ተቋም እንዲኖራት ለማድረግ አባላቶቻችንን የአካዳሚ እና ወታደራዊ ሥልጠናዎችን በማሰልጠን ላይ የም ንገኝ ሲሆን ፥ ለኢትዮጵያ ከባህርም ሆነ ከየብስ የሚቃጡ አደጋዎችን የሚመክት ብቁና ጠንካራ የባህር ሃይል አባላት በመገንባት ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
መከላከያ የባህር ሃይል ሰልጣኞችን በውጤታማነት አሰልጥኖ በማስመረቅ ለሠራዊታችን ተጨማሪ አቅሞችን እንደሚፈጥር እተማመናለሁ ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.