Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሂሩት ካሳው ወሎ ግንባር በመገኘት የትህነግ ሃይልን እየታገሉ ያሉ የመከላከያ ሰራዊትን አበረታቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በወሎ ግንባር ፍላቄት ከተማ በመገኘት ለሀገር ህልውና መስዋዕትነት እየከፈሉ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊትን አበረታተዋል፡፡
እንዲሁም በግንባሩ ከሚገኙ ጀኔራሎች ጋር በቀጣይ ከአመራሩ የሚጠበቀውን ሚና እና ድጋፍ ፤ በህልውና ዘመቻው ሂደት ከህብረተሰቡና ከአመራሩ በሚጠበቀው ድርሻ ዙሪያ ተወያይተዋል።
ጀኔራሎቹም የህብረተሰቡና የወጣቶች ደጀንነት በስንቅ ዝግጅት እየተደረገ ያለው ድጋፍ ታሪክ የሚዘክረው መሆኑን ገልፀው ÷በዚህም መደሰታቸውን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ዶክተር ሂሩት ካሳው ለሴት መከላከያ ሰራዊት የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ፣በፍላቄት ከተማ ለሚገኙ እናቶችና ህፃናት የሚውል ሃይልሰጭ ብስኩትና ማካሮኒ ድጋፍ አድርገዋል።
ድጋፉንም መቄት ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ መረከባቸውን ከደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.