Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ጎንደር ዞን መከላከያ ሰራዊቱን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ጎንደር ዞን የሃገር መከላከያ ሰራዊቱን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ።

በደብረታቦር ዩኒቨርስቲ ከሁሉም የዞኑ ወረዳዎች የተውጣጡ ወጣቶች እና ጎልማሶች በትልቅ ሃገራዊ ወኔ ሽኝት ተደረጎላቸዋል።

በሽኝቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ምልምል ወታደሮች በርካታ እንግዶች በተገኙበት ወደ ማሰልጠኛ ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

የደቡብ ጎንደር አስተዳዳሪ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ እንደገለጹት÷ የሽብር ቡድኑ በውጪ ወራሪዎች እየታገዘ የኢትዮጵያን አንድነት ለመበታተን ቆርጦ በመነሳት የተለያዩ ጥፋቶችን አድርሷል።

በዚህ ሂደት ኢትዮጵያዊያን የበለጠ የብረት አጥር የሆኑበት፤ ሀገርን ከጥፋት ለመጠበቅ በአንድነት በመነሳትም የደቡብ ጎንደር ወጣቶች ማሳያ ናቸው ብለዋል።

‘’የትህነግ የሽብር ቡድን የፈጠረውን መሰባሰብ እንደ ምቹ አጋጣሚ በመቁጠር በመከላከያ ሰራዊቱ ተቀላቅላችሁ የሚሰጣችሁን ስልጠና በብቃት በመወጣት የላካችሁን ህዝብ የሚመጥን እና የአባቶቻችሁን ገድል ፈፃሚ እንድትሆኑ’’ ሲሉ መክረዋል።

የአማራ ክልል መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ÷ ኢትዮጵያ ከውስጥም ከውጭም የተደቀነባትን ወራሪ ሀይል በዚህ ነበልባል ወጣት ይመከታል ብለዋል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት አባል እና የብሄራዊ ጀግኖች አምባ አማካሪ ብርጋዴር ጄኔራል ካሳየ ጨመዳን ጨምሮ የክልል እና የዞን አመራሮች ባለሃብቶች የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት ሽኝት ተደርጓል።

በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.