Fana: At a Speed of Life!

የባህላዊ ወርቅ አምራቾች የሮያሊቲ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ተነሳ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህላዊ መንገድ ወርቅ እያመረቱ ለባንክ ለሚያቀርቡት አምራቾች ለክልል ሲከፍሉ የነበረው የሮያሊቲ ክፍያን ሙሉ በሙሉ መነሳቱ ተገለፀ።
የመዐድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የሚመሰገን ውሳኔ ብለዉ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸዉ ላይ እንዳሰፈሩት የሮያሊቲ ክፍያዉ ተነስቷል ።
የሚሰሩ ጠንካራ እጆች ሁሌም ድጋፍ ይገባቸዋል።የባህላዊ እና አነስተኛ ወርቅ አምራቾቻችን ለሀገራችን የማዕድን ክፍለ ኢኮኖሚ ዋልታ ሆነው ዘመናትን እያሻገሩን ይገኛሉ ብለዋል ሚኒስትሩ።
እነሱን በተለያየ መንገድ መደገፍ ፣ከትከሻቸው ላይ ጫናዎችን ማቃለል ከእኛ የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው።
የክልሎቻችን ርእሰ መስተዳድሮች በባህላዊ መንገድ ወርቅ እያመረቱ ለባንክ ለሚያቀርቡት አምራቾች ለክልል ሲከፍሉ የነበረውን የሮያሊቲ ክፍያን ሙሉ በሙሉ አንስተዋል።
ይህ እርምጃ ለባህላዊ የማዕድን ምርት እንደሀገር የሰጠነው ትኩረት ማሳያ ነው።
በሌላ መልኩ ደግሞ በህገወጥ መንገድ የሃገር ሀብት ላይ አሻጥር ለሚሠሩት ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
አጥፊዎችን እየቀጣን፣ የሚሰሩትን እየደገፍን ጉዟችንን እንቀጥላለን።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
69,905
People Reached
4,019
Engagements
Boost Post
1.3K
31 Comments
35 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.