Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣መስከረም 11 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት እያካሄደ ነው።
ውይይቱም በዋናነት የኢሬቻ በዓል በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር የባለድርሻ አካላት ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑንም ተገልጿል።
ለፓናል ውይይት የመወያያ ጽሑፍ ያቀረቡት ዶክተር ብርሃኑ ባይሣ እንዳሉት ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው።
ኢሬቻ የእርቅ፣ የወንድማማችነት እና የመተሳሰብ በዓል መሆኑንም አስረድተዋል።
የኦሮሞ ህዝብ የክረምት ወቅትን አልፎ ወደ ጸደይ ወራት ያደረሰውን ፈጣሪ የሚያመሰግንበት ክብረ በዓል መሆኑንም ገልጸዋል።
ዘንድሮ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ሁሉንም ብሔር ብሔረሰቦች ባሣተፈ መልኩ እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል።
ኢሬቻ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት በዓል በመሆኑ ትውፊቱን ጠብቆ መከበር እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
እየተካሄደ በሚገኘው የፓናል ውይይትም አባገዳዎች፣ ሃደ ሲቄዎች፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ ወጣቶችና ሴቶች በመሣተፍ ላይ ይገኛሉ ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.