Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ሴክተር አመታዊ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሴክተር ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።

በጉባኤው የ2013 በጀት አመት አፈጻጸም ግምገማና የዕውቅናና ማበረታቻ ስነ ስርዓት ፣የመንግስት አገልግሎት ዘርፍ ፍኖተ ካርታ የቀጣይ 10 አመታት መሪ ዕቅድ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም የ2014 በጀት አመት ዕቅድን አስመልክቶ የክልል፣የዞንና የወረዳ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ምክክር ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.