Fana: At a Speed of Life!

ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የታላቁ የህዳሴ ግድብን ጎብኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምድር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከፍተኛ የመንግስት የሰራ ሃላፊዎች እና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች የታላቁ የህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ለፕሮጀክቱ መሳካት እየተከናወነ ያለውን እረፍት አልባ የሰራዊቱ የግዳጅ አፈፃፀም ያደነቁ ሲሆን ምስጋናም አቅርበዋል።

ጀኔራል መኮንኑ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት ÷የህዳሴውን ግድብ ፕሮጀክት ለማደናቀፍ ማሰብ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ጉዳይ እንደማይደራደሩ በቅጡ ካለመረዳት የሚመነጭ ስሕተት ነው።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል የሚቀሳቀሱ የውክልና ጦር አስፈፃሚዎች ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚንቀሳቀሱ ቅጥረኛ ሃይሎች አይሳካላቸውም ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.