Fana: At a Speed of Life!

ኢንዱስትሪያል ፓርኩ 114 ሚሊየን ዶላር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለውጭ ገበያ ከላካቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል 114 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ አገኘ።

የፓርኩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍጹም ከተማ ፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የ2013 ዓ.ም ለዘርፉ ስራ ከባድ ጊዜ ብለዋል።

መንግስት የተለያዩ አማራጮችን በማመቻቸት አምራች ካምፓኒዎች ጫናዎችን ተቋቁመው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ለማስቻል ከፍተኛ ጥረት በመደረጉ ጥሩ ውጤት ተመዝግቧል ነዉ የተባለዉ።

ከዚህ ቀደም 20 የውጭ ባለሀብቶች ቦታ ወስደው ምርት ላይ እንደነበሩ ያስታወሱት ዋና ስራ አስኪያጁ ፤የኢንዱስትሪ ፓርኩ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ተሳትፎ እየጨመረ መምጣቱንም አስረድተዋል።

ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያነት የሚውሉ ጥራት ያላቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችና ሌሎች ምርቶችን በማምረት የቫይረሱን ክስተት ወደ መልካም አጋጣሚ መቀየር ችለናል ብለዋል።

23 ካምፓኒዎች ስራ ላይ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ፍጹም÷ አሁን ላይ ሶስት የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ሼድ ወስደው ወደ ምርት ሂደት መግባታቸውን ተናግረዋል።

የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ከ35 ሺህ በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ ዕድል መፍጠሩም ተመልክቷል።

ፓርኩ ባለፈው በጀት ዓመት ለአውሮፓና አሜሪካ ገበያ ካቀረበዉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል 114 ሚሊየን ዶላር ገቢ አግኝቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.