Fana: At a Speed of Life!

በጂንካ ከተማ የተገነባው የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ታወር ተመረቀ

አዲስ አበባ፣መስከረም 11፣2024 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ የተገነባው የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ታወር ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የታወሩ መገንባት በጂንካ አየር ማረፊያ አማካይነት የሚሰጠውን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ቀልጣፋ÷ ዘመናዊና ደህንነቱ የተረጋገጠ በማድረግ ረገድ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ካሳሁን ጎፌ ተናግረዋል፡፡

በምረቃ ስነስርዓቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌን ጨምሮ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲ እንዲሁም ከፍተኛ የፌዴራል፣ የክልልና የዞን የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸዉ ታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.