Fana: At a Speed of Life!

በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ448 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 448 ሺህ 550 የአሜሪካ ዶላር ተያዘ።
ቢራ በመጫን መነሻውን ከአማራ ክልል ደብረብርሃን ከተማ ያደረገው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-26981 ኢት.ተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪ አዲስ አበባ ከተማ ከደረሰ በኋላ ወደ ሀረር ከተማ በማቅናት ላይ እያለ ቃሊቲ ኬላ ላይ በተደረገበት ፍተሻ በህገ-ወጥ መንገድ ሲያጓጉዘው ከነበረ ከ448 ሺህ 550 የአሜሪካ ዶላር ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ገለፀ፡፡
በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረው ዶላር ሊያዝ የቻለው ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ጥብቅ ክትትልና ፍተሻ ሲሆን፥ አሽከርካሪው ዶላሩን በቢራ ሳጥን ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር ነው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬከቶሬት ከፀረ-ኮንትሮባንድ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር ያዋለው።
በወንጀሉ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለው አሽከርካሪ ከነዶላሩ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ተላልፎ ጉዳዩ በምርመራ ሂደት ላይ መሆኑም ታውቋል።
አሸባሪው የህወሓት ጁንታ ቡድን ቀድሞ በዘረጋቸው ኔትዎርኮች አማካኝነት በንግድ ተቋማት የሚሰበሰብ ዶላርን በሀገ-ወጥ መንገድ በውድ ዋጋ እየገዛ ከሀገር እንዲወጣ እና በሀገር ውስጥ የዶላር እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
ከዚያም ባለፈ ከዚህ የሚያገኘውን ገቢ ለሽብር ተግባር መፈፀሚያ የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ እንዲያገለግለው ሲሰራ መቆየቱን ተነግሯል ፡፡
ይህንን ለመከላከል ፖሊስ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመቀናጀት ባካሄደው ኦፕሬሽን በጥቁር ገበያ ላይ የሚንቀሳቀሰው ህገ-ወጥ የዶላር ምንዛሪ እየቀነሰ መምጣቱን አንዳንድ የሚዲያ ተቋማት ባካሄዱት የዳሰሳ ጥናት ያረጋገጡ መሆኑን ገልፀዋል።
በአሸባሪው የህወሃት ጁንታ ቡድን አባልነት የሚጠረጠሩ አንዳንድ ግለሰቦች አሁንም ከድርጊታቸው ያልተቆጠቡ መሆኑን ባደረገው ክትትል ማረጋገጡን የገለፀው ፖሊስ፥ በቃሊቲ ኬላ ዶላሩ ሊያዝ የቻለው በህብረተሰቡ ትብብር በመሆኑ መረጃውን ላደረሱ ግለሰቦች ታላቅ ምስጋና አቅርቧል።
በቀጣይም ህብረተሰቡ ተመሳሳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ከህግ አስከባሪ አካላት ጎን በመሰለፍ፣ ጥቆማ በመስጠትና መሰል ህገ-ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲል መልዕክት ማስተላለፉን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
387
Engagements
Boost Post
336
24 Comments
27 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.