Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል በዓልን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክስቲያን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መጪውን የመስቀል በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክስቲያን አስታወቀች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከፊታችን ለሚከበረው የመስቀል በዓል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከወዲሁ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፋለች፡፡

የቤተክርስቲያኗ ጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅ ቀሲስ በላይ መኮንን÷ ምዕመናን የመስቀል ደመራ በዓልን ሲያከብሩ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የመስቀል ደመራ በዓል ከቀደሙት በተለያዩ ምክንያቶች ልዩ ያደርገዋል ያሉት ቀሲስ በላይ÷ ባለፈው ዓመት በኮቪድ 19 ምክንያት በመስቀል አደባባይ ጥቂት ሰዎች ተገኝተው በዓሉ መከበሩን አስታውሰዋል፡፡

አሁን ግን የኮቪድ 19 ቫይረስን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና ጥንቃቄ በማድረግ ማህበረሰቡ ተገኝቶ በድምቀት የሚያከብረው ይሆናል ነው ያሉት፡፡

ሌላው በአሁኑ ጊዜ የመስቀል አደባባይ ግንባታ ተጠናቆ ባማረ መልኩ እንድናከብር ስለተመቻቸ ልዩ ያደርገዋል ያሉት ቀሲስ በላይ መኮንን÷ ለዚህም መንግስትን አመስግነዋል፡፡

የመስቀል ደመራ በዓል በዓለማችን በማይዳሰሱ ቅርስነት መመዝገቡን አውስተው÷ በዓሉን በተለያዩ አካባቢዎች ስናከብር በሠላም፣ በፍቅር እና በመተሳሰብ መሆን አለበትም ብለዋል፡፡

በቅድስት ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.