Fana: At a Speed of Life!

ለመከላከያ ዋር ኮሌጅ ውጤታማ የሠራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ዋር ኮሌጅ ውጤታማ የስራ አፈፃጸም ለነበራቸውና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የሠራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ተሰጠ፡፡

የኮሌጅ ዋና አዛዥ ሜ/ጄ ሃብታሙ ጥላሁን ባስተላለፉት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም÷ ኢትዮጵያ በትልቅ ደረጃ በምትፈልግበት ወቅት ላይ ለተጨማሪ ሃላፊነትና ሹመት በመብቃታችሁ ለተሿሚዎችና ለተሿሚ ቤተሰቦች እንኳን ደስ ያላችሁ ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የማዕረግ ሹመት የሚሰጠው በነበራቸው የስራ ሃላፊነት መንግስትና ህዝብ የሰጣቸውን ተልዕኮዎች በላቀ ደረጃ በመፈፀማቸው ጥሩ ስራ ሰርተዋል የሚል እውቅና መስጠት እንደሆነም ሜ/ጄ ሃብታሙ ገልጸዋል፡፡

‘’ለቀጣይም የበለጠ ሰርታችሁ፣ እውቀታችሁን አዳብራችሁ አካላዊ ብቃታችሁን የበለጠ አጠናክራችሁ የሚጠበቅባችሁን ተግባር በላቀ ሁኔታ ትፈፅማላችሁ የሚል መተማመን በመስጠት በአደራም ጭምር የሚሰጥ ማዕረግ ነው’’ ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.