Fana: At a Speed of Life!

ቡና ባንክ ለመምህራን እና ለጤና ባለሞያዎች ያዘጋጀውን የሎተሪ እጣ አወጣ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቡና ባንክ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው መምህራንን እና የጤና ባለሞያዎችን ተሳታፊ ያደረገው የሎተሪ እጣ መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም በብሄራዊ ሎተሪ በዕድል አዳራሽ በህዝብ ፊት በይፋ ወጥቷል፡፡
ይህ የሃገር ባለውለታዎችን ለማስታወስና የቁጠባ ባህልን ለማዳበር ታልሞ በባንኩ የተዘጋጀው የመምህራን እና የጤና ባለሞያዎች የመጀመሪያው ዙር ፕሮግራም በሁሉም ደረጃ ላይ የሚገኙ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎችን ተሳታፊ ያደረገ አዲስ የቁጠባ መርሃ ግብር ነው፡፡
የቡና ባንክ ስትራቴጂ ዋና ኦፊሰር አቶ መንክር ሃይሉ የእጣ አወጣጥ ስነስርአቱን በይፋ ሲከፍቱ፥ ትምህርትና ጤና የአንድ ሃገር የዕድገት ማስቀጠያ ምሰሶዎች ናቸው ብለዋል።
ሃገር ጤናማ ስርዓት ገንብታ ወደዕድገት የምታመራው አንድም በዕውቀት የታነጸ ፣ በሌላ በኩልም ጤናው የተጠበቀ ዜጋ ሲኖራት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ትውልድን በእውቀት የማነጽ እና የህዝብን ጤና የመጠበቅን ከባድ ሃላፊነት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚሸከሙ ምሰሶዎች መሆናቸውን ቡና ባንክ በጽኑ ያምናል ብለዋል፡፡
ባንኩ እነዚህ የሃገር ባለውለታዎች አንድም የቁጠባ ባህላቸውን እያሳደጉ የባንኩ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፣ በሌላ በኩልም በመቆጠባቸው ብቻ ተሸላሚ መሆን የሚችሉበት መርሃ ግብር ዘርግቷል።
በዛሬው እለት በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ በተካሄደው የእጣ ማውጣት ስነስርአት የምእራብ መርካቶ ቅርንጫፍ ደንበኛ የሆኑት መምህር የ2020 ሞዴል ሱዙኪ ዲዛየር መኪና አሸናፊ ሆነዋል፡፡
በየደረጃው ለሽልማት የተዘጋጁ 12 ላፕቶፖች፣ 12 ታብሌቶች፣ 24 ስማርት የሞባይል ስልኮች እንዲሁም 6 የእረፍት ጊዜ ሽርሽር ሙሉ ወጪ የተሸፈነላቸው የታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት ፓኬጆች ለእድለኞች መድረሳቸውን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.