Fana: At a Speed of Life!

መገናኛ ብዙሃን ግንባር በመገኘት የሚሰሯቸው ዘገባዎች የሽብር ቡድኑን እውነተኛ መልክ እያሳየ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በጦር ግንባር በመገኘት የሚሰሯቸው ዘገባዎች እውነታን በማውጣትና የህወሓት የሽብር ቡድኑንን እውነተኛ መልክ በማሳየት ላይ እንደሚገኙ በዘገባ የተሳተፉ ባለሙያዎችና የጦር መኮንኖች ተናገሩ፡፡

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኛ ዙፋን ካሳሁን ከጀግኖች ጋር ውሎ በማደር ለህዝቡ እውነተኛ መረጃን ማድረስ ሙያዊ ሀላፊነትን መወጣት እንደሆነ ተናግራለች፡፡

በግንባር በነበራት ቆይታ የኢትዮጵያ ሰራዊት ስለሀገር ውድ ዋጋን ሲከፍል፣ ድልንም ማግኘት ሲችል መመልከቷን የተናገረችው ዙፋን አሁንም ግን ቡድኑ በተሸነፈባቸው አካባቢዎች ሰብዓዊ ቀውሶችን መፈፀሙን ተናግራለች፡፡

በአፋር ግንባር ቆይታ ያደረገው ጋዜጠኛ አወል አበራ በበኩሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ግንባር ድረስ ዘልቀው መስራታቸው በተለይም መርጦ አልቃሽ የሆኑት የውጭ መገናኛ ብዙሃን የተዋቸውን ድምፆች ማሰማት እንደተቻለ አንስቷል፡፡

መገናኛ ብዙሃን የሽብር ቡድኑን አስነዋሪ ተግባራት በማጋለጥ ሚና ነበራቸው ያሉት ጋዜጠኖቹ ከጋሊኮማ እስከ ጭና ያሉ የሽብር ተግባራትም መቅረባቸውን አውስተዋል፡፡

ሆኖም የተጀመረው ስራ ውጤት በማምጣት ላይ ቢሆንም በቂ የሚባል አይደለም እንደ ጋዜጠኞቹ ገለፃ፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ አድማሱ ዳምጠው ÷ባለሙያዎቹን በተለያዩ ግንባሮች በማሰማራት ስራዎችን እየሰራ ሲሆን ይህም ፋና ካለበት ሀገራዊ ግዴታ የሚመነጭ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

መገናኛ ብዙሃን እውነትና እውቀትን መሰረት አድርገው መስራት እንዳለባቸውም የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚው እንዲሁም ሀገርን በማስቀደም መስራት አለባቸው፤ሀገርን ያስቀደመ እውቀት መር አሰራር ያስፈልጋል ሲሉም አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

ሁሉም አበርክቶው የሚያስፈልግበት ወቅት መሆኑ ታውቆም የሙያን የማበርከት ግዴታ እንዳለም አክለዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በበኩላቸው÷የህወሃት ቡድን በየቀኑ ሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳን እንደሚያሰራጭ ገልፀው ከዚህ ጋር የሚመጣጠን እውነታውን መረጃ የሚያቀርብ የመገናኛ ብዙሃን ስራ መስራት እንደሚጠይቅ አንስተዋል፡፡

የመገናኛ ብዙሃን እስከ አውደውጊያዎች የዘለቀ ስራ የሙያ ብቻ ሳይሆን የሀገርን ልዕልና ስለማስጠበቅ የተደረገ ታሪካዊ ሀላፊነትን ስለመወጣት የሆነ ነው፤ግን ከዚህም የተሻገረ ቀጣይ ስራዎችን ይጠይቃል ብለዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ፋይናንስ መምሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ዓለምሰገድ ወንድወሰን ÷የመገናኛ ብዙሃን ስራዎችየህዝቡን ደጀንነት ከማሳደግ፣ የሀሰት ፕሮፖጋንዳን ከማጋለጥ በዘለለ በሰራዊቱ አባላት ላይ መነቃቃትን በመፍጠርና ወደ መከላከያ የሚቀላቀሉ ዜጎች ቁጥር እንዲጨምር አወንታዊ ሚና መጫወቱን አንስተዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.