Fana: At a Speed of Life!

በማይጠብሪ በህወሓት ወረራ ለተፈናቀሉ ዜጎች የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሰሜን ጎንደር ዞን በህወሓት ወረራ ለተፈናቀሉ ዜጎች የእርዳታ ድርጅቶች እና ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉ የዞኑ ምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት ጥሪ አቀረበ።

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ በለጠ ጥላዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ በሰሜን ጎንደር ዞን በሽብር ቡድኑ ህወሓት ወረራ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከቀን ቀን እየጨመረ ነው።

አሁን ላይም በዞኑ ከሚገኙ 6 ወረዳዎች ከ80 ሺህ እስከ 100 ሺህ የሚደርሱ ተፈናቃዮች መኖራቸውን ነው የገለጹት።

በጦርነቱ አጠቃላይ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ቁጥርም 582 ሺህ በላይ ደርሷል ነው ያሉት።

የአለም የምግብ ፕሮግራም በአራት ወረዳዎች በትህነግ ወረራ ለተፈናቃሉ ዜጎች የምግብ ነክ ቁሳቁስ አቅርቦት ማሰራጨት መጀመሩን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጅ በጠለምት እና አዲ አርቃይ ወረዳዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች የእርዳት አቅርቦት እየተዳረሰ አለመሆኑን አንስተዋል።

በተለይም የምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች አቅርቦት ችግር ከፍተኛ መሆኑን ነው የገለጹት።

ስለሆነም የእርዳታ ድርጅቶች እና የመንግስት ተቋማት እንዲሁም ባለሃብቶች ለተፈናቃይ ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመላኩ ገድፍ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.