Fana: At a Speed of Life!

የቁሳቁስ ስርጭት ስራ ተጠናቋል-ቦርዱ

አዲስ አበባ፣መስከረም 11፣2024 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለድምፅ መስጫና ለኦፕሬሽን ሥራዎች የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ከማዕከል ወደ ምርጫ ክልሎች አሰራጭቶ ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ቦርዱ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በሐረሪ ፣ ሶማሌ እና ደቡብ ክልል ለሚያካሂደው ምርጫና ሕዝበ ውሣኔ ለድምፅ መስጫና ለኦፕሬሽን ሥራዎች የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ነው ከማዕከል ወደ ምርጫ ክልሎች አሰራጭቶ ያጠናቀቀው፡፡

ሥርጭቱ መስከረም 7 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጀመረ ሲሆን ÷ሐረሪ ፣ ሶማሌ እና ደቡብ ክልል ላይ የሚሠራጩትን ቁሳቁሶች የጫኑ መኪኖች አዲስ አበባ ከሚገኘው የቦርዱ ጊዜያዊ መጋዘን መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደየ ምርጫ ክልል ተንቀሳቅሰው ጨርሰዋል ተብሏል።

በአዲስ አበባና ቅርብ አካባቢዎች ለሐረሪ ተወላጆች ለተከፈቱት ምርጫ ጣቢያዎች የሚሠራጩትን ቁሳቁሶች ደግሞ የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች መድረስ ያለበትን የጊዜ ርዝማኔ ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የሚጠናቀቅ መሆኑን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.