Fana: At a Speed of Life!

የሰሜን ወሎ ዞን ነዋሪዎች የዕለት እርዳታው የቤተሰቦቻችንን ሕይወት ታድጓል አሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ወሎ ዞን ነዎሪዎች የዕለት እርዳታ በማግኘታቸው የቤተሰቦቻቸውን ሕይወት መታደግ እንደቻሉ ገለጹ።

ነዎሪዎቹ እንደገለጹት÷ ጁንታው የዕለት ምግብ እንኳ እንዳይኖር አድርጎ ጥፋት ቢያደርስም በአካባቢው እርዳታ በመምጣቱ አሁን ላይ የዕለት ደራሽ እርዳታ ማግኘት መቻላቸውን ተናግረዋል።

እርዳታው በ ዮኤስ ኤይድ አማካኝነት የቀረበ ሲሆን÷ ደብሊውኤፍፒ በማጓጓዝ እንዲሁም የአማራ መልሶ ማቋቋም ድርጅት (አመልድ) ድጋፉን በማድረስ ላይ ይገኛሉ።

በዛሬው እለትም ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ስንዴ ዘይትና አተር ክክ በነፍስ ወከፍ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው የሕብረተሠብ ክፍሎች የሁለት ወር እርዳታ ማግኘታቸውን ገልጸው÷ ዘላቂነት እንዲኖረው ጠይቀዋል።

የውርጌሳ ከተማ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ እንድሪያስ ፈንታው እንደተናገሩት÷ አሁን ላይ ከወልዲያ፣ ከመርሳ እንዲሁም ከሀራ ገበያና ከሌሎች የሰሜን ወሎ ዞን አካባቢዎች የመጡ የሕብረተሠብ ክፍሎች ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ድጋፉም ለሁሉም ተጎጂዎች እንዲደርስ ርብርብ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

በቅርቡ መንግስት ከረጂዎች ጋር በመተባበር ግጭት ባለበት አከባቢ እርዳታ ለማድረስ ይሰራል ማለቱ የሚታወስ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.