Fana: At a Speed of Life!

በጁንታው አካባቢያችንን ሳናሰደፍር ቆይተናል- የውርጌሳ ወጣቶች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጁንታው እኛን አልፎ ደቡብ ወሎ ዞን ለመግባት ጥረት ቢያደርግም በጋራና በአንድነት በመቆማችን አካባቢያችንን ሳናሰደፍር ቆይተናል ሲሉ የውርጌሳ ከተማ ወጣቶች ገለጹ።
በውርጌሳ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሪፖርተሮች ጋር ባደረጉት ቆይታ ጁንታው የውርጌሳ አከባቢውን ለመቆጣጠር በርካታ ሰላዮችን ወደ ከተማው በመላክ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካለትም ብለዋል።
ሽብር ቡድኑ ውርጌሳ ከተማን ለመቆጣጠር ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ቢያደርግም በጸጥታ ሀይሉና በወጣቱ ቅንጅት ሳይሳካለት ቀርቷል ነው ያሉት።
የጋዜጠኛቹ ቡድን በስፍራው ባደረገው ቅኝት ውርጌሳ ከተማና አካባቢዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው መመለሷን ተመልክቷል። ግጭቱን ሸሽተው ተፈናቅለው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችም ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን አረጋግጧል።
ወጣቶቹ እንደተናገሩት ሰርጎ ገብ ወደ አከባቢያቸው እንዳይገባ ከመጠበቅ ባለፈ ከጸጥታ ሀይሉ ጋር በመቀናጀት ጁንታውን ለማጽዳት እየሠሩ ነው።
የውርጌሳ ከተማ አመራር የሆኑት አቶ ንጋቱ ሞላ በበኩላቸው ጁንታው ከ15 በላይ ሰላዮችን ቢልክም አንዱም ሳይመለሱ ለመከላከያ ሰራዊት ገቢ ሆነዋል ብለዋል።
አሁን ላይ አከባቢው ሰላማዊ ነው ያሉት አቶ ሞላ፥ ማህበረሰቡን በማስተባበር ለወረራ፤ ግድያና ዝርፊያ የተሰማሩትን የጁንታውን አባላት ባሉበት መቅበር ቀጣይ ስራችን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በከድር መሀመድና በሀብታሙ ተክለስላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.