Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን እየተጋፈጠ የሚያሸንፍ ማንነት ነው –  ብ/ጀ አስፋው ማመጫ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊነት ፈተና የበዛበት ነገርግን ፈተናን እየተጋፈጠ የሚያሸንፍ ማንነት መሆኑን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ብ/ጀ አስፋው ማመጫ ገለጹ።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት በስሩ ለሚገኙ 95 የሰራዊት አባላት የማዕረግ እድገት ሰጥቷል ፡፡

ይቺ ታላቅ ሀገር በጀግኖች አባቶቻችን ታፍራ ፣ ተከብራ ፣ ስሟ እንዳማረ ፣ በጠላቶቿ እንደተፈራች ፣ የአለም ጥቁር ህዝቦች ሞዴል ሆና እዚህ ደርሳለችም ነው ያሉት፡፡

ሀብታም ስለሆንን ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት የተለየና አውቀን ያልጨረስነው በወርቅ የተለበጠ የአትንኩኝ ባይነት ማንነት ስለሆነ ነው  ፡፡

ስለሆነም የዛሬ ተሿሚዎች ይህንን የአበው የጀግንነት ውርስ በተግባር ለማዋል ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ተልዕኳችን ጊዜን ዕውቀትን ፣ ጉልበትን ፣ ህይወትን የሚጠይቅ በመሆኑ ፣ ዛሬ ኢትዮጵያ ማዕረግ የሰጠቻችሁ ከተጨማሪ አደራ ጭምር በመሆኑ ሀላፊነታችሁን ከትናንት በተሻለ ብቃት መወጣት ይጠበቅባችኋል ብለዋል ፡፡

በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ፣ የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ሀላፊ ተወካይ ብ/ጀ መኮንን አስፋው ፣ የመከላከያ ሰላም ማስከበር ሎጀስቲክስ መምሪያ ሀላፊ ብ/ጀ ጠቅለው ክብረት ፣ የመከላከያ ሚዲያ ዳይሬክተር ብ/ጀ ኩማ ሚደቅሳ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ መኮንኖች ማዕረግ ማልበሳቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.