Fana: At a Speed of Life!

ኮሜዲያን ማርቆስ ፍቅሩ እና የቦሌ ቡልቡላ ወረዳ ወጣቶች በደሴ ከተማ ለተጠለሉ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦርቢል ፕሮሞሽን ባለቤት ኮሜዲያን ማርቆስ ፍቅሩ እና በአዲስ አበባ ከተማ የቦሌ ቡልቡላ ወረዳ ወጣቶች በደሴ ከተማ ለተጠለሉ ተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ።
ድጋፉ ከ640 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የምግብና እና የቁሳቁስ ደጋፍ መሆኑ ነው የተገለጸው።
አሸባሪው የትህነግ ቡድን በአማራ ክልል በፈጸመው ወረራ ከሰሜን ወሎ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖች በደሴና ሌሎች ከተሞች ተጠልለው ይገኛሉ።
በኮሜዲ ሥራዎቹ የሚታወቀው የኦርቢል ፕሮሞሽን ባለቤት ኮሜዲያን ማርቆስ ፍቅሩ ከቦሌ ቡልቡላ ወረዳ ወጣቶች ጋር በመተባበር ደሴ ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃዮችን ጎብኝተው ድጋፍ አድርገዋል።
ኮሜዲያን ማርቆስ ለወገኖቹ ከጎናቸው መሆኑን ለማሳየት እና ያሉበትን ሁኔታ ለመመልክት መገኘቱን ገልጾ ፡ወደፊትም የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግሯል።
ተፈናቃዮች ከሞቀ ቤታቸው ተሰደው ያሉበት ሁኔታ አሳዛኝ ነው ያለው ኮሜዲያን ማርቆስ፥ “እኛ የቻልነውን እናደርጋለን፣ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን በተመሳሳይ ለመርዳት እንሠራለን” ሲል ቃል ገብቷል።
ኮሜዲያን ማርቆስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እነዚህን ተፈናቃዮች የመርዳት ኢትዮጵያዊ ሃላፊነት እንዳለበትም ተናግሯል። ይህ ድጋፍ እንዲሳካ ለተባበሩት እና ለቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ወጣቶች ምስጋና ማቅርቡን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.