Fana: At a Speed of Life!

ትራንስፖርት ሚኒስቴር እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስምምነት ሰነዱን የተፈራረሙት የትራንስፖርትሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ እና የአለም ምግብ ፕሮግራም ድርጅት በኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር እስቲቨን ዌር ናቸው፡፡
ስምምነቱ መንግስት የሀገሪቱን የሎጂስቲክስ ዘርፍ ለማቀላጠፍ የሚያደርገዉን የአቅርቦት ዕዝ ሰንሰለት ማሻሻል ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም በትራንስፖርት ሚኒስቴር የ10 ዓመት መሪ ልማት ዕቅድ የተቀመጡ የብሄራዊ የሎጀስቲክስ ስትራቴጂ ግቦችን ለማሳካት ያግዛል መባሉን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ስምምነቱ የትራንሰፖርት ዘርፉን በምርምርና ቴከኒክ ድጋፍ፣ በሰዉ ሀይል አቅም ግንባታና የሎጂስቲክስ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረዉም ተመላክቷል፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የአለም ምግብ ፕሮግራም ድርጅት ስምምነቱን በመፈራረም ወደፊትም በጋራ ለመሰራት ስላለው ዝግጁነት አመስግነዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
42
Engagements
Boost Post
41
1 Share
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.