Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከጋቦን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የጋቦን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓኮሜ ሞቤሌት ቡቤያ በኒውዮርክ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በውይይቱ የኢትዮጵያ እና ጋቦን የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ተነስተዋል።

በቅርቡ ጋቦን ወደ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ቀጣይ አባል መሆኗን ተከትሎ÷ ለአፍሪካውያንን ድምፅ በመሆን ሚናዋን እንደምትወጣ ዕምነታቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ገልፀዋል።

የፀጥታው ምክር ቤት በአፍሪካ ቀንድ ያለው ትኩረት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱን በመጥቀስ÷ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካውያን መፍትሄ እንዲያገኙ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው በአፅንኦት ተናግረዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ እና ጋቦን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.