ዶ/ር አረጋና ቤተሰቦቻቸው በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶክተር አረጋ ይርዳውና ቤተሰቦቻቸው ከሰሜን ወሎ የተለያዪ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደሴ ከተማ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉ የምግብ እህል አልባሳት እንዲሁም የቤት ቁሳቁስን ያካተተ ሲሆን÷ በቅዳሜ ገበያ ትምህርት ቤት ለተጠለሉ ተፈናቃዮች መድረሱም ተገልጿል፡፡
ድጋፉን ያደረጉት ዶክተር አረጋ÷ ሀገር ከችግር ትወጣ ዘንድ ሁሉም በአቅሙ ሊደግፍ ይገባል ብለዋል።
የተፈናቃዮቹ ሁኔታ ልብ የሚነካ በመሆኑ÷ ሁሉም በአለው አቅም ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
ዶክተር ይህ ድጋፍ የመጀመሪያ ዙር መሆኑን ጠቁመው÷ በቀጣይም ተጠነክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
በከድር መሀመድ እና በሀብታሙ ተክለስላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!