Fana: At a Speed of Life!

እርዳታ አቅርቦቱ ትግራይ እርዳታ ለማድረስ ሄደው ባልተመለሱ ተሽከርካሪዎች ሳቢያ ተስተጓጉሏል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)እርዳታ ለማድረስ ትግራይ ክልል ሄደው በዛው የቀሩ ተሽከርካሪዎች አለመመለስ በእርዳታ አቅርቦቱ ላይ ችግር መፍጠሩን የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ገለጹ።

የእርዳታ እህል ጭነው ወደ ትግራይ ከሄዱ 466 ተሽከርካሪዎች 428ቱ ከትግራይ ክልል አለመውጣታቸው የእርዳታ አቅርቦቱ ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ይገኛል ሲሉ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ይህን እኩይ ተግባር ማውገዝ አለመቻሉም ችግሩ የከፋ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል።

ኮሚሽነሩ ከአንድ የሀገር ውስጥ ሚድያ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ጠቅሶ ኢፕድ እንደዘገበው÷ የግለሰብ ንብረት የሆኑና በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ሚና እየተጫወቱ የነበሩ 428 ተሽከርካሪዎች የእርዳታ እህል ጭነው ወደ ትግራይ ክልል በሄዱበት እዛው መቅረታቸው ጉዳት እያስከተለ መሆኑን አስረድተዋል።

ለመኪኖቹ አለመመለስ ምክንያት የሆነው የነዳጅ እጥረት ነው ሲል ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን ያቀረበው ምክንያት ተቀባይነት የለውም ያሉ ሲሆን÷ በቂ ነዳጅ ወደክልሉ እንዲገባ መደረጉንም ገልጸዋል።

ከትግራይ ክልል ያልወጡ መኪኖች በአፋጣኝ ተመልሰው ወደክልሉ የእርዳታ ቁሳቁሶች ማድረስ የሚጠበቅባቸው ናቸው ያሉት ኮሚሽነሩ፣ በትግራይ ክልል ለሚከሰት ረሃብ የፌዴራል መንግሥት በኃላፊነት ሊጠየቅ አይገባም ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.