Fana: At a Speed of Life!

ከ80 በላይ የመንገድ መብራት የብረት ምሰሶዎች አገልግሎት ባለመስጠታቸው ነዋሪዎች ቅሬታ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ከ80 በላይ የመንገድ መብራት የብረት ምሰሶ ተተክሎ አገልግሎት መስጠት ባለመቻሉ የቡራዩ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታ አቀረቡ።

በቡራዮ ከተማ ከታ ቀበሌ ከዓመታት በላይ ያለ አገልግሎት የቆመ የመንገድ መብራት ለብልሽት እና ለስርቆት እየተዳረገ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ይህም በዕለት ተዕለት ኑሯአቸው ላይ በተለይ ከስራ አምሽቶ ለመግባት ችግር እንደሆነባቸው ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል።

ያለ አገልግሎት የቆመው የብረት ምሰሶ ብዙ ወጭ ወጥቶበት መሆኑን ነዋሪዎቹ ጠቁመው÷ ይህ አግባብ እንዳልሆንም አንስተዋል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡን የቡራዮ ከተማ አስተዳደር የማዘጋጃ ቤት ጽህፈት ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አብዲሳ ዱጉማ ለጣቢያችን እንደገለጹት÷ በተደጋጋሚ ለቡራዮ ከተማ ኤሌክትሪኩ አገልግሎት እንደማይሰጥ በደብዳቤ ብናሳውቅም ምንም ምላሽ አልተሰጠም ይላሉ።

የክትትል ችግር በመኖሩ በወቅቱ ችግሩን ለመቅርፍ እንዳልተቻለ እና እስከ ታህሳስ 2014 ዓም አገልግሎት እንዲስጥ እንደሚሰራ ምክትል ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቡራዮ ከተማ ዲስትሪክት የደንበኞች አገልግሎት ስራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ድንቁ በበኩላቸው÷ በጉዳዩ ላይ ማንም አካል የጠቆመንም ሆነ በደብዳቤ የጠየቀን አካል የለም ነገር ግን ጉዳዩን ተከታትለን ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋግረን መስመሩ አገልግሎት እንዲስጥ ይደረጋል ብለዋል።

በሲሳይ ጌትነት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.