Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ለ15 ዓመታት የሚቆይ የአውሮፕላን ቁሳቁስ ጥገና ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ቁሳቁስ ጥገናን በጋራ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከሳናድ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር ተፈራረመ።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ አየር መንገዱ የጥገና ስራዎችን ከአቡዳቢው ኩባንያ ጋር በትብብር ለመስራት መስማማቱን ገልጸዋል።

ለቀጣዮቹ 15 ዓመታት የሚቆየው ይህ ስምምነት እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ አቪዬሽን ኮንፈረስ ውጤት ነው ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚው።

የጣምራ የጥገና ትብብሩ የአየር መንገዱን ቴክኖሎጂና ልምድ ለማሳደግና ለማሻሻል እንደሚያግዝም ጠቁመዋል።

የሳናድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መንሱር ጃንሀዲ በበኩላቸው ÷ በአፍሪካ የመጀመሪያው በሆነው ትብብር ደስተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሀይለየሱስ መኮንን

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.