Fana: At a Speed of Life!

በ10 ሚሊየን ዶላር ለሚገነባው የመድሀኒት ፋብሪካ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቂሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ የመድሀኒት እና የህክምና ቁሳቁስ ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

የመሰረት ድንጋዩ አፍሪቱር ፋርማኪዩር ማኑፋክቸሪንግ የኢንቨስትመንት ስራውን በኢንዱስትሪያል ፓርኩ ለመጀመር የሚያስችለው ነው ተብሏል።

ፋብሪካው በ10 ሚሊየን ዶላር ወጪ የሚገነባ ሲሆን፥ በ18 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባም በአመት ከአንድ ቢሊየን በላይ በአፍ የሚወሰዱ እንክብል መድሀኒቶችን እና 14 ሚሊየን ሽሮፕ መድሀኒቶችን የማቅረብ አቅም አለው ተብሏል።

ፋብሪካው ከመቶ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ሲሆን፥ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ባለሃብቶች ሽርክና የሚገነባ ነው።

ከህክምና መድሃኒቶች ባለፈም የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ያመርታል።

በፀጋየ ንጉስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.