Fana: At a Speed of Life!

የሁርሶ ሰልጣኞች ለሃገራቸው ዘብ ለመቆምና መስዋእትነት ለመክፈል ቁርጠኞች መሆናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁርሶ በሰላም ማስከበር የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሰረታዊ ውትድርና እየሰለጠኑ ያሉ ምልምሎች ለሃገራቸው ዘብ ለመቆምና መስዋእትነት ለመክፈል ቁርጠኞች መሆናቸው ተገለፀ።
የሁርሶ ኮንቴንጀንት መሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮ/ል አዲሱ ተርፋሳ ፥በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ምልምሎች የውስጥና የውጭ ጠላቶችን ለመመከት የሚያስችላቸውን ወታደራዊ ሰልጠና በከፍተኛ የሀገር ፍቅርና ወኔ እየተከታተሉ ይገኛሉ።
የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ም/አዛዥ ስልጠና ሃላፊ ኮ/ል አሊ ሰይድ ፥ አሸባሪና ከሀዲ ቡድኖች ሀገር ለማፍረስ ቢታትሩም ሀገርን ከመፍረስ ለመታደግ ከሁሉም የሀገራችን አቅጣጫ የተመሙ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት ነፃ በሆነ መንገድ በሀገራዊ ፍቅርና ስሜት ፣ በወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ብቻ እንዲሰለጥኑ እየተደረገ እንደሚገኝ ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.