Fana: At a Speed of Life!

“በአባቶቻችን ደም እና አጥንት የተገነባች ሀገራችንን ለወራሪ ጠላት አሳልፈን አንሰጥም” – የደሴና አካባቢው ወጣቶች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴና የአካባቢው ወጣቶች ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ጋር በመሆን አሸባሪውን የትህነግ ኃይል ለመደምሰስ ወደ ግንባር መዝመታቸውን ገልጸዋል።
ወጣቶቹ አሸባሪው የትህነግ ኃይል በአማራ ላይ እየፈጸመ ያለው ግፍ እንዲያበቃ ወደ ግንባር በመዝመት ወራሪው ኃይልን ባለበት ለመቅበር በፍፁም ቁርጠኝነትና ወኔ ነው ወደ ግንባር የዘመቱት።
ወጣት ጌታቸው ሳህሉ የግንባር ስምሪቶችን በመቀበል ወጣቶች ወደ ጦር ግንባር ወርደው መከላከያ ሠራዊትን፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ተቀላቅለው ወራሪውን ለመቅበር መዝመታቸውን ተናግሯል።
“በአባቶቻችን ደም እና አጥንት የተገነባች ሀገራችንን ለወራሪ ጠላት አሳልፈን አንሰጥም” ያለዉ ወጣት አሊ አህመድም ጠላትን ለመደምሰስ ወደ ግንባር መዝመቱን ይናገራል።
“የጠላትን የጥፋት ሴራ እናመክናለን፤ ሀገራችንን ለማንም አሳልፈን አንሰጥም ብለን ወጣቶች በመሰባሰብ ወደ ግንባር ዘምተናል” ያለው ወጣት አሊ÷ ከመከላከያና ከልዩ ኃይል ጋር በመሆን አካባቢያቸውን ከሰርጎ ገብ እንደሚያፀዱም ገልጿል።
ሌላው ወጣት ተረፈ አልብሴ በበኩሉ÷ የወራሪው ትህነግ ግፍን እንዳየ ገልጾ ሌላ ተጨማሪ ግፍ እንዳይፈፀም
ከአካባቢው ወጣቶች ጋር ተቀናጅቶ ጠላትን ባለበት ለመፋለም መዝመቱን ተናግሯል።
የደሴ ከተማ ወጣት ሰርጎ ገቦችን በመቆጣጠር ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቁርጠኝት ሲሠሩ መመልከቱን የገለፀው ተረፈ÷ከመከላከያ ሠራዊትና ከአማራ ልዩ ኃይል ጋር በመሆን ጠላትን ለመቅጣት ከደሴና ከአካባቢው ወጣቶች ጋር አብሮ ወደ ግንባር መዝመቱን ገልጿል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.