Fana: At a Speed of Life!

ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ስለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ የሚመክር ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሙና አህመድ እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያ በአፍሪካ በአንፃራዊነት በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት አንዷ በመሆኗ ፈጣን እድገት እያሳየ ካለው ህዝብ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወጣቶች ሥራ አጥ ናቸው፡፡

ባለፉት ዓመታትም የሥራ አጥነት መጠን እየጨመረ መሆኑንም ወይዘሮ ሙና ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በከተሞች ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ሥራቸውን በተለያዩ ዘርፎች ስራ ለመፍጠር የሚያስችል ክህሎቶችን እያስተዋወቀ እንደሚገኝና ተደራሽነቱንም ለማሳደግ ያለውን ተነሳሽነት አስረድተዋል።

ሚኒስትሯ መንግስት ስራ አጥነትን ለመከላለክል የሰራቸውን ስራዎችና በቀጣይ የታቀዱ ዕቅዶችን አብራርተዋል፡፡

ትናንት የተጀመረው ስለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ የሚመክረው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ዛሬም ቀጥሎ እንደሚውል ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.